በጀት ዓመቱ በክህሎት ልማት ዘርፍ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች የምንሰራበት ነው፡፡ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ
January 30, 2025

በጀት ዓመቱ በክህሎት ልማት ዘርፍ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች የምንሰራበት ነው፡፡
ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያለፉት ስድስት ወራት የክህሎት ልማት ዘርፍ ስራዎች አፈጻጸም የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ( ዶ/ር) ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት እና የየክልሉ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት እየተገመገመ ይገኛል፡፡
ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) መድረኩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት በጀት ዓመቱ ዘርፉን ወደ ፊት የሚያስፈነጥሩ የተለዩ ስራዎች የምንሰራበት እና የጀመርናቸው የሪፎርም ስራዎች የምናጸናበት ነው ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦች እየተፈጸሙ የሚገኝበት አግባብ ለማየት የድጋፍና ክትትል፣ ቨርቿል እና አስቸኳይ የገጽ ለገጽ መድረክ በመጥራት ውይይቶች መደረጋቸውን ገልጸው ይህ መድረክም ከቦታ ቦታ የሚታዩ የአፈጻጸም ልዩነቶችን ለማጥበብ፣ እቅዶቻችንን ዳግም ለማየት እና የቀሪ ስድስት የወራት የዘርፉ የርብርብ ማዕከል አጀንዳዎችን በመለየት ወደ ስራ ለመግባት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል፡፡
ዘርፉ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው የተቀመጡ አካባቢያዊ ጸጋን መነሻ ያደረገ ስልጠና መተግበር፣ የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማጠናከር፣ ቲቬት ድጅታላይዜሽን፣ የማሰልጠኛ ተቋማት የውስጥ አቅም ማጠናከር፣ የአይሶ ትግበራ፣ ጥራት ያለው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስልጠናዎች መስጠት የመሳሰሉት ስራዎች ልዩ ትኩረት የሚፈልጉ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

















