Mols.gov.et

በጀርመኗ ላይፕዚግ የደመቀው የእንጦጦዋ ፍሬ …

August 26, 2024
በጀርመኗ ላይፕዚግ የደመቀው የእንጦጦዋ ፍሬ … አዲስ አበባ በጀርመኗ ላይፕዚግ ከተማ አደባባይ እንደተሰየመላትና በሁለቱ የእህትማማች ከተሞች አጋርነት 20ኛ ዓመት የማክበር ስነ-ስርዓት ላይ ተመርቆ ስለመከፈቱ ተዘግቧል፡፡ በታሪካዊቷ የላይፕዚግ ከተማ ይህ አደባባይ መሰየሙ በሁለቱ ከተሞች ብቻ ሳሆን በሀገራቱ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር ነው፡፡ ለመሆኑ የሁለቱ የእህትማማች ከተሞች መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነ የተነገረለት ይህ አደባባይ ላይ የቆመው ሀውልት የተቀረፀው በማን ነው? የሚል ጥያቄ አንስተው ከሆነ መልሱ ወደ አዲስ አበባ ይመልስዎታል፡፡ ፍሬሽወይን እንድሪስ ትባላለች፡፡ በታሪካዊው እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኤስቴቲክስ ስልጠና ዘርፍ የስነ-ውበት ሠልጣኝ ናት፡፡ ባለፈው ዓመተት በጀርመኗ ላይፕዚግ ከተማ በተካሄደው የሰዓሊያን ውድድር ላይ ተካፍላለች፡፡ በዚህም በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ 25 ተወዳዳሪዎች መካከል 1ኛ በመውጣት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች፡፡ እንሆ ዛሬ አሸናፊ የሆነችበት የጥበብ ሥራዋ የሁለቱ ከተሞችን አስተሳስሮ በላይፕዚግ ከተማ በኩራት ለመቆም ችሏል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፍሬሽወይን እንድሪስን ሥራዋ ከፍ ባለ ደረጃ በመቀመጡ እንኳን ደስ ያለሽ ለማለት ይወዳል። በክህሎት ልማቱ ላይ እየሰጡት ላለው ቁርጠኛ አመራር ለውጥ እያመጡ በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን፣ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮን እንዲሁም የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክን ኮሌጅ አመራርና ባለሙያዎች በሙሉ ምስጋና ይገባቹኋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top