በክላስተር ደረጃ የሚካሄደው የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ውድድርና ኤግዚቢሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በድምቀት ተጀመረ
‹‹ብሩህ አዕምሮዎች፤ የተፍታቱ እጆችና በክህሎት የበቁ ዜጎች›› በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በክላስተር ደረጃ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ውድድርና ኤግዚቢኑን በድምቀት እየተካሄደ እንደሚገኝ ከክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውድድሩ ላይ አሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳዎች የማበረታቻ ሽልማት የተዘጋጀላቸው ሲሆን ክላስተሩን በመወከል ለክልላዊ ውድድር እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡
በየክላስተሩ የሚካሄዱት ሁነቶች ለጉብኚዎች ክፍት በመሆናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በሥፍራው በመገኘት ኤግዚቢሽኖቹን እንዲጎበኙና ተወዳዳሪዎችን እንዲያበረታቱም ጥሪ ተላልፏል፡፡