Mols.gov.et

በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ደቡብ ሱዳን የአውስትራሊያ አምባሳደር ጋር…

April 2, 2025
በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ደቡብ ሱዳን የአውስትራሊያ አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ፒተር ሃንተር ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነታችን በምናሳድግበት ሁኔታዎች ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ በውይይቱ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀረፁ የልማት ፖሊሲዎችንና የተገኙ ውጤቶችን አይተናል፡፡ በክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም ሥራ ዕድል ፈጠራና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ዘርፉ ላይ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም ሥራዎችንም በዝርዝር ተመልክተናል፡፡ ኢትዮጵያና አውስትራሊያ የክህሎት ልማት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን ጨምሮ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያልቁ የትብብር መስኮች ላይ በቅንጅት ለመሥራት ተግባብተናል፡፡ ይህም ረዥም ጊዜ ያስቆጠረውን የሁለትሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድገው ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ፒተር ሃንተር በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡ የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
en_USEN
Scroll to Top