በአዲስ አባባ ሲካሄድ የነበረው የክህሎት ውድድር ተጠናቀቀ
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ15ኛው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት አንዱ አካል የሆነው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር “ብሩህ አዕምሮዎች ፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ቃል በከተማዋ በሚገኙ ኮሌጆች በስድስት ክላስተር ተካሂዷል።
በቢሮው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ኢንኩቤሽን አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ በየነ እንደገለፁት፣ ውድድሩ በ19 የሙያ አይነቶች በ104 ሰልጣኞች መካከል ተካሂዷል።
የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ዕድገት በክህሎት በማዳበር እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የዘርፉን ዕድገት በማሳደግ ሂደት የክህሎት ውድድሩ ሚናው ጉልህ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በክላስተር የተካሄደው የክህሎት ውድድር መጠናቀቁን ተከትሎ የውድድሩ አሸናፊዎች በቀጣይ ከተማ ደረጃ በሚካሄደው የክህሎት ውድድር እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡