Mols.gov.et

በበጀት ዓመቱ የማጠቃለያ ምዕራፍ የክልሎች አቅም የማጠናከር ሥራ በትኩረት ይሠራል። ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ

April 9, 2025
በበጀት ዓመቱ የማጠቃለያ ምዕራፍ የክልሎች አቅም የማጠናከር ሥራ በትኩረት ይሠራል። ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡ በግምገማው በዘጠኝ ወሩ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና ከኢንዱስትሪ ግንኙነትና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር አንፃር የተከናወኑ ዝርዝር ሥራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የተቀናጀና የተናበበ ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ ከአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት አንፃር የተያዙ ዕቅዶችን ከማሳካት አንፃር ከፍተኛ መሻሻሎች መኖራቸውን የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታው ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ የወሳኝ ቦርድ አደረጃጀትን በክልሎች ማስፋትና የሙያ ደህንነትና ጤንነትን ጉዳይ በሁሉም የሥራ ቦታዎች ሜይንስትሪም ማድረግ የሚያስችል ንቅናቄ መፍጠር የዘርፉ የቀሪ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ ጠቁመዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የማጠቃለያ ምዕራፍ የክልሎችን አቅም የማጠናከር ሥራ በትኩረት እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top