በሥራ ዕድል ፈጠራው ዘርፍ የፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ከአዋሽ ባንክ ጋር ተፈራርመናል፡፡
ስምምነቱ በርካታ ዜጎችን ባጠረ ጊዜ ወደ ሥራ ለማስገባት ያስችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር የኢመደበኛ ንግዶችን ወደ መደበኛ ለማሸጋገር የተጀመረውን ጥረት የሚያግዝና በቅንጅት በሚሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የኢንተርፕራይዞችን የመክሰም ምጣኔን ለመቀነስ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
በውስጥ አቅም በልጽጎ ሥራ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በመስኩ አገልግሎት ለሚሰጡ የፋይናነስ ተቋማት ትልቅ የመወሰን አቅም የሚፈጠር ነው፡፡ በመሆኑም በሥራ ዕድል ፈጠራ ስነ-ምህዳር ግንባታው ላይ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ የቆየውን የፋይናንስ አቅርቦትን ለመፍታት በዘርፉ የሚገኙ ተቋማት የአዋሽ ባንክን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪዮን ለማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡
የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ፀሀይ ሽፈራው እና መላው የተቋሙ አመራሮች በመስኩ ፋዋና ወጊ የሆነ ሥራ ከመስራት ባሻገር ሥራውን ለማላቅ ከተቋማችን ጋር በትብብር ለመሥራት ላሳያችሁን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!