Mols.gov.et

በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል፡፡

March 27, 2025
በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከ”ለነገዋ” የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የሥራ ኃላፋች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶችን ተጠቃሚነት ማላቅ ላይ ባተኮረው የውይይት መድረክ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሂርጳሳ ጫላ እና ም/ል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤልሻዳይ ክፍሌ ተገኝተዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፤ በማዕከሉ የሚሰለጥኑ ሴቶች በሥራ ገበያው ላይ ተፈላጊ የሆነ ክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማላቅ ይሰራል፡፡ በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ ያሉ ዕድሎችን እንዲጠቀሙ ከማድረግ ባሻገር የማዕከሉን አቅም ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲያድግ ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ብለዋል፡
en_USEN
Scroll to Top