Mols.gov.et

በልምድ ያገኙትን ክህሎት በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠቱን ማዕከሉ አስታወቀ

January 30, 2025
በልምድ ያገኙትን ክህሎት በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠቱን ማዕከሉ አስታወቀ የሐረሪ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በልምድ ያገኙትን ክህሎትና ብቃት በምዘና ላረጋገጡ ባለሙያዎች እውቅና መስጠቱን አስታውቋል። በማዕከሉ እውቅና የተሰጣቸው የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች እንደሆነም ተጠቁሟል። የማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ በዳሳ ገመዳ በኢትዮጵያ ከመደበኛ ሥልጠና ውጪ የሙያ ባለቤት የሆኑ በርካታ ባለሙያዎች አሉ። በልምድ የተገኙ እውቀቶችን እውቅና በመስጠት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ብልፅግና ትልቅ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ማድረግ ይገባል ብለዋል። በልምድ የተገኘ ክህሎት በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠት የዜጎችን የራስ መተማመን ለማሳደግ እንዲሁም አካታችነትን እና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የላቀ መሆኑንም አመላክተዋል። ማዕከሉ በክልሉ የሚኖሩ ዜጎች ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት ለማድረግ እየሰራ ነው ተብሏል:: በቀጣይም በተለያዪ ሙያዎች እውቅና የመስጠት ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለፁት።
en_USEN
Scroll to Top