Mols.gov.et

በሀገራችን የመጀመሪያው የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ሊዘጋጅ ነው።

January 30, 2025
በሀገራችን የመጀመሪያው የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ሊዘጋጅ ነው። መዝገበ ቃላቱን የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ መሆኑ ተጠቁሟል። ሁለቱ ተቋማት መዝገበ ቃላቱን በትብብር ለማዘጋጀት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለፁት፣ ኢንስቲትዩቱ ለረጅም ዓመታት በስልጠና ፣ በጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ለዘርፋ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱን አውስተዋል። ከመዝገበ ቃላት ዝግጅቱ ባለፈም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በቀጣይነት እንሰራለን ብለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ለሀገራችን ቱሪዝም ዘርፍ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክተውን የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ለማጠናቀቅ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብለዋል። የኢትዮጵያ ቋንቋና ባህል ልማት ኢንስቲትዩት ደይሬክተር ዶ/ር ዮሐንስ በበኩላቸው፣ መዝገበ ቃላቱ ለሀገራችን ቱሪዝም እድገት አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በኩል ወደ 4000 የሙያ ቃላት መሰብሰቡን ተናግሯል ።
en_USEN
Scroll to Top