Mols.gov.et

ስምምነቱ በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን ማላቅ የሚያስችል እንደሆነ ተገለፀ፡፡

March 16, 2025
ስምምነቱ በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን ማላቅ የሚያስችል እንደሆነ ተገለፀ፡፡ በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስት መካከል የተደረገውን የድጋፍ ስምምነት ወደ ሥራ ማስገባት የሚያስችል የሚያስችል የስትሪንግ ኮሚቴ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱን ተከትሎም ፕሮጀክቱን ወደ ሥራ ማስገባት የሚያስችል የትግበራ ስምምነት ተፈርሟል፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰብሳቢነት የመጀመሪያውን የስትሪንግ ኮሚቴ ውይይት መድረክ ዝርዝር ማስፈፀሚያ ዕቅድ ያፀደቀ ሲሆን ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስርዓት በመዘርጋት ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይገባል ሲሉ በአፅንዎት አሳስበዋል:: በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስት መካከል የተደረገው የድጋፍ ስምምነት በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን ማላቅ የሚያስችል የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ያካተተ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል፡፡ ፕሮጀክቱ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ለስምምነቱ ስኬት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ምስጋ አቅርበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top