Mols.gov.et

ስልጠናው ህገ-መንግስታዊ ተግባራትን በብቃትና በእውቀት መውጣት የሚያስችል ነው። የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ -ጉባኤ

May 18, 2025
ስልጠናው ህገ-መንግስታዊ ተግባራትን በብቃትና በእውቀት መውጣት የሚያስችል ነው። የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ -ጉባኤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተሰጠው የፐብሊክ ኢንተርፕርነር እና የፈጠራ ስነ-ምህዳር ግንባታ ስልጠና ለምክር ቤቱ የተሰጡ ህገ መንግስታዊ ተግባራትን በብቃትና በእውቀት መውጣት የሚያስችል መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ አስገንዝበዋል። የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ይህን ያሉት ለሦስት ተከታታይ ቀናት ለምክር ቤት አባላት ሲሰጥ የቆየው የፐብሊክ ኢንተርፕርነር እና የፈጠራ ስነ-ምህዳር ግንባታ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ነው። ምክር ቤቱ የተሰጡትን ተግባራት ሲያከናውን ለአዳዲስ ሀሳቦችና ፈጠራዎች ተኩረት በመስጠት አደናቃፊና አሳሪ የሆኑ ሕጎችን ማሻሻልና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የሚያስችለው አቅም የፈጠረ መሆኑም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንሶች የሚካሄዱበት ሀገር በማድረግ በተጨባጭ አቅሞቻችንን እና እድሎቻችንን ተጠቅመን ፈጣን እድገት ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ብለዋል። የሥልጠናው ተሣታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው ለአገራችን ማበርከት ያለብንን አስተዋፅዖ ያመላከተ፣ ያለንን ሀብት አውቀን እንዴት መጠቀም እንዳለብን ያሳየ እንደሆነ ገልፀዋል። እንደ ሀገር በምናከናውናቸው ልማታዊ ተግባሮቻችን ውስጥ ማነቆ የሆኑ ነገሮችን በመፍታት አገር መቀየር የሚያስችል እውቀት ያገኙበት እንደሆነም አመላክተዋል። ስልጠናው ከመቼውም ጊዜ የተለየና ተግባር ተኮር መሆኑ መነሳሳት እንደፈጠረባቸው የገለጹት የምክር ቤቱ አባላት፤ በዚህ በየጊዜው ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ውስጥ እንደዚህ ያለ ወቅቱን የዋጀ ስልጠና በጣም አስፈላጊ እንደሆነም ነው የጠቆሙት። እንደ ኢንተርፐርነር ልማት ኢንስቲትዩት ያለ ለአገር አድገት ተቆርቋሪ የስልጠና ማዕከል በአገራችን መቋቋሙ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ የበለጠ እንዲጠናከር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው፣ የፐብሊክ ኢንተርፐርነር እና የፈጠራ ስነ-ምህዳር ግንባታ ስልጠና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መስጠቱ ህዝብን እንደማሰልጠን ይቆጠራል። ስልጠናው ቀፍድደው ከያዙን ልማዳዊ አስተሰሰቦች ወጥተን አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን በማፍለቅ ወደ ሀብት መቀየር የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል። የልጆቻችን ህልም እንዲሳካ መስራት እና ህገ-መንግስታዊ ተግባሮቻችንን በእውቀት መምራት ይጠበቅብናል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ይህን ካደረግን የኢትዮጵያ የመልማት ህልም የሚሳካበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ማለታቸውን የምክርቤቱ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
en_USEN
Scroll to Top