Mols.gov.et

ሰመር ካምፕ ችግር ፈቺና ሀብት አመንጪ የሆኑ ፈጠራ የታከለባቸው ቴክኖሎጂዎች ማምረት የተቻለበት ነው ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

September 7, 2024
ሰመር ካምፕ ችግር ፈቺና ሀብት አመንጪ የሆኑ ፈጠራ የታከለባቸው ቴክኖሎጂዎች ማምረት የተቻለበት ነው ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ኢንተርፕሪነርሺፕ ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ‹‹ሠመር ካምኘ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ›› የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ አስጀምረዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት አምና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ላለፉት 12 ወራት ተኪ ምርቶችን የማምረት ሥራ በስፋትና በጥራት በሰመር ካምኘ ተሳታፊዎች ሲሰራ ቆይቷል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተወጣጥተውና በዓንድ ማዕከል ተሰባስበው ባለፈው አንድ ዓመት የፈጠራ ሥራቸውን የማዳበር ሥራ ሲሰሩ የቆዩት ወጣቶች ፋብሪካ ማምረት ጀምረዋል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ይህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን እራስን የመቻል ጉዞ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። የሰመር ካምኘ ተሳታፊዎች በ11 ዘርፎች 81የሚሆኑ እጅግ ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎች ማምረታቸውን ጠቁመው እነዚህ ፈጠራዎች በስፋት ተመርተው ለገበያ እንዲቀርቡ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
en_USEN
Scroll to Top