Mols.gov.et

#ለ2ኛ ዙር የሠመርካምፕ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር ምዝገባ ተጀመረ።

September 4, 2024
#ለ2ኛ ዙር የሠመርካምፕ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር ምዝገባ ተጀመረ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ያዘጋጁት በአይነቱ ልዩ የሆነ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልጸጊያ መርሃ ግብር ወጣቶች የፈጠራ ሐሳባቸውን እና ችሎታቸውን ወደ ተጨባጭ ሥራ እንዲለውጡ በማስቻል ለአገራችን ሁለንተናዊ እድገት ትልቅ አበርክቶ ያላቸው ቴክኖሎጂዎች ማስገኘት የሚያስችል ነው። በዚህ መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል። ስለሆነም በማንኛውም መስክ የቴክኖሎጂ እና የሥራ ፈጠራ ሐሳብ ያላችሁ በሙሉ ከነሐሴ 27/2016 ዓ/ም ጀምሮ ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ እንድትመዘገቡ ተጋብዛችኋል። https://forms.office.com/r/CNMFUUSZZe #ማሳሰቢያ 📌 ምዝገባው የሚካሄደው በተቀመጠው ድህረገጽ ብቻ ነው 📌ከምዝገባ በኋላ በሚካሄድ ልየታ መሠረት ለሚመረጡ የፈጠራ ባለሙያዎች የሠመር ካምፕ ፕሮግራሙ የሚካሄደው አዲስ አበባ ላምበረት መነሀሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋናው ካምፓስ ነው።
en_USEN
Scroll to Top