Mols.gov.et

ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

July 26, 2024
ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ የደቡብ ኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ላለፉት አምስት ቀናት ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል። በስልጠናው ማጠቃለያ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ደቡብ ኮሪያ ቴክኒክና ሙያን ከእድገታቸው ጋር አስተሳስረው በመሥራታቸው በዘርፉ ስኬት ማስመዝገባቸውን ገልጸው አመራሩ በዚህ ስልጠና ያገኙትን እውቀትና ልምድ ለሀገራችን በሚሆን መልኩ መተግበር እንዳለባቸው አሳስበዋል። መንግስት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና ጥራት የሚያሻሽሉ የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን የጠቆሙት ሚ/ር ዴኤታው መሰል ድጋፎች ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትን ለማሻሻል እያደረገ የሚገኘው የግብዓት እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን በመገለጽ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ኮርያና ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ፣ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ትምህርትና ሌሎች ዘርፎች ለይ በአጋርነት እየሰሩ መሆኑንም ተገልጿል።
en_USEN
Scroll to Top